የባህር ሃይል መልሶ ማቋቋም ና የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍሎ የማይጨርሰው እዳ

ከሰሞኑ ከወደ ሃገር ቤት የምንሰማቸው አስፈሪና አሳፋሪ ዜናዎች አብዛኛውን የመገናኛ ብዙሃን የአየር ጊዜ ቢቆጣጠሩትም፣ እንደ ዋዛ ተነግሮ ያለፈው የኢትዮጵያን የባህር ሃይል የማንሰራራት እቅድ የደረሰበትን ደረጃና እነማን የውጭ ሃገራት ጣልቃ ገብነት እንዳለበት ከምን ግዜውም በበለጠ ግልጽ እየሆነ ነው። ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት እንደመንደርደሪያ እንዲሆን ስለቀደመው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የመጨረሻ ይውድቀት ጊዚያቶች እንመልከት።

ኤርትራ ነጻነቷን ካወጀች በኋላ፣ ኢትዮጵያ እራሷን የባህር በር አሳጥታ ወደብ አልባ ሃገር ሆነች። የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ግን ለተወሰኑ አመታት በመደነባበር እራሱን ለማቆየት ሞክሮ ነበር። ዋናው የባህር ሃይል ኮማንድ ቢሮው አዲስ አበባ ላይ ቢቆይም፣ ከአዲስ አበባ በሚሰጥ ትዕዛዝ የጦር መርከቦቹ መቆያቸውን የመን አድርገው በቀይ ባህር ላይ ፓትሮል ያረጉ ነበር። በኋላም የመን መርከቦቹን ስታባርር አብዛኛዎቹ መርከቦች (ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ ጀልባዎች ቢሆኑም ለዚህ ጽሁፍ ግን መርከቦች እያልን እንጠራቸዋለን) ከመበላሸታቸው የተነሳ ወደ ባህር የመውጣት ብቃት አልነበራቸው። ስለዚህም የባህር ሃይሉ መርከቦቹን የመን ትቶ ወጣ። አንጋፋዋ ኢትዮጵያ የሚል ስም ያላት የጦር መርከብ የመን ስደርስ አቋሟ ጥሩ ስላልነበረ በ1993 እኤአ ተሽጣለች (ኢትዮጵያ የተባለችው የጦር መርከብ በ 1942 እኤአ የተሰራችና በ 1962 እኤአ ከአሜሪካ ባህር ሃይል በውሰት መጥታ በ1976 እኤአ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የገዛት ናት)። ሌሎች መርከቦችና ጀልባዎችም ከየመን መውጣት ያልቻሉት ተሽጠዋል ወይም እንዲሰምጡ ተደርገዋል።

ከወደብ መውጣት የቻሉት ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ እንዲሄዱ ተደርገዋል። የባህር ሃይሉ ወደ ጅቡቲ ሲመጣ እድሜው የሚረዝም መስሎ ነበር። በውቅቱ በጅቡቲና በኤርትራ ወደቦች ለማቆየት ታስቦም ነበር። ምንም እንኳን ጅቡቲ በወቅቱ ፈቃደኛ ብትሆንም፣ ኤርትራ ግን የራሷን የባህር ሃይል የማቋቋም ህልም ስለነበራት የኢትዮጵያን መንግስት ጥያቄ አልተቀብለችም። መርከቦቹን ለሁለት ለመካፈል እና በሁለቱ ሃገራት ባህር ሃይሎች ከኤርትራ ወደቦች የጦር መርከቦቹን ለማንቀሳቅስ ሃሳብም ቀርቦ ነበር። አሁንም በህይወት ያለው የኤርትራ መንግስት ግን የራሱ አሻጥር ስለነበረው ይህንንም ሃሳብ አልተቀበለውም።

ከሶስት አመታት የጥገኝነት ቆይታው በኋላም፣ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ከጅቡቲ አዲስ ፈተና መጣበት። የወደብ እዳውን መክፈል አቃተው በሚል ምክንያት በ 1996 እኤአ ጅቡቲ ወደብ ውስጥ የቀሩትን መርከቦች አግታ በሃራጅ እንዲሸጡ ወሰነች። ምንም እንኳን ኤርትራ በወቅቱ 16ቱን መርከቦች ለመግዛት ፍላጎት ብታሳይም፣ በኋላ ግን አራት ብቻ ገዛች። የተቀሩት መርከቦች ግን ለብረታቸው ሲባል እንዲቆራረጡ ተሽጠዋል። በዚሁ አመት በ 1996 እኤአ አዲስ አበባ መሰረቱን ያደረገው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል እንዲፈርስ ተደርጓል። የተቀረው ታሪክ ነው።

ከ2 አስርተ አመታት በኋላ በታሪክ አጋጣሚ ይሁን ወይ እናቱ ባዩለት ትንቢት አብይ አህመድ የተባሉ ሰው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ። ጠ/ሚ በሆነ በሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ያስፈልጋታል ብለው ንግግር አደረጉ። ስለባህርና ስለመርከብ የሚያቁትን ሳይጨምር የሚመጣው እዳ ያልተረዳ ህዝብ እንደሌሎቹ መሳጭ ንግግሮች ከመቀመጫው ብድግ ብሎ አጨበጨበ። ሃሳቡ ሳይሆን ያመጣው ጭብጨባ በፈጠረው ስካር እነሆ ከአመት ከመንፈቅ በኋላ እውነትም የኢትዮጵያ ባህር ሃይል እንደገና ሊያንሰራራ ብዙ እንቅስቃሴዎች በይፋ እየተነገሩ ነው።

ከሰሞኑ በመገናኛ ብዙሃን ከምንሰማው በመነሳት፣ ጅቡቲ ወደብ ለባህር ሃይሉ ማረፊያ እንደሚዘጋጅ፣ ባህር ዳር ጣና ላይ ዋናው ኮማንድ እንደሚቀመጥ፣ ፈረንሳይ ና ኖርዌይ የገንዘብና ተያያዥ እርዳታ እንደሚያደርጉ፣ ስለጣኞች ውደ ራሽያ እንደተላኩ፣ የምድር ጦር አባል የሆነ ብርጋዴል ጀነራል የባህር ሃይል አዛዥ ሆኖ እንደተመረጠ፣ የመሳሰሉት።

ጅቡቲ

ጅቡቲን ማስተዋወቅ አያስፈልግም። ቢያንስ ኤርትራ ከተገነጠለች በኋላ ከ 90% በላይ የኢትዮጵያን የወጭ ገቢ ንግድ በባህር በርነት የምታስተናግድ ሃገር ናት። ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በፊት በአማራጭነት ብቻ የምናያት ጅቡቲ፣ በአሁን ሰአት በኢትዮጵያ ገንዘብ ከምንምነት ወደ አካባቢው ወሳኝ ሃገርነት/ወደብነት የተሸጋገረች ሃገር ናት። ከንግድ መርከቦች፣ ወደብ ኪራይና በየጊዜው በሚጨምረው ቀረጥ በተገኘ ገንዘብና ባላት መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ በአሁን ሰአት ደግሞ የተለያዩ ሃገር የባህር/ጦር ሃይል ማሳረፊያ ቦታዎችን ከፋፍላ በመቸብቸብ ከስድስት በላይ የውጭ ሃገራት የጦር መርከቦች የሚመላለሱባት ሃገር ናት። በአጭሩ የጅቡቲ ኢኮኖሚ የተመሰረተው ወደብ በማከራየትና የተለያዩ ሃገራትን የጦር ሃይሎች በማስተናገድ ነው።

ጅቡቲ የኢትዮጵያን የባህር ሃይል ለማስተናገድ ስትስማማ መታየት ያለበት ከዚሁ የገንዘብ ጥማቷ ጋር በማቆራኘት ብቻ ነው። ለኢትዮጵያ አዝና ወይም የወዳጅነት ውጤት አይደለም። ማናልባትም ልክ ንግድ መርከቦቻችን ላይ እንዳደረገችው በመጀመሪያ አጉዋጊ ጥቅማ ጥቅሞችን ካሳየችን በኋላ የባህር ሃይሉ ብዙ ወጭ ከወጣበትና ወደሌላ ቦታ ማንቀሳቅስ አማራጭ እንደሌለን ስትረዳ፣ ከአቅማችን በላይ የሆነ ክፍያ እንደምትጠይቅ እርግጠኛ ነኝ። ይህ በግዜ የሚታይ ጉዳይ ቢሆንም፣ ለወደብ ኪራይና ተያያዥ ወጭዎች ከምንም የሚቆጠር ባይሆንም እንኳን የባህር ሃይል ምልሶ ማቋቋሙ ለኢትዮጵያ እንደሃገር ኪሳራ እንጅ የሚያመጣው ጥቅም እንደሌለ ከዚህ በታች ለማብራራት እሞክራለሁ።

ሃገሪቷ ላይ የሚያስከትለው የኢኮኖሚ እዳ

በአሁኑ ወቅት እንደምንረዳው የፈረንሳይ መንግስት በዋናነት፣ የኖርዌይ መንግስት በተጨማሪ የባህር ሃይሉን ለማንሰራራት እገዛ እንደሚያደርጉ በተለያዩ ሜዲያዎች እየተነገረ ነው። የባህር ሃይል የአንድ ጊዜ ኢንቨስትመንት አይደለም። ‘’እገዛ’’ የሚለው ለሚዲያ በሚመች መልኩ ይመር እንጂ የተወሰነው እገዛ የሚመጣውም በብድር መልክ ነው። በተለይ ፈረንሳይ ባህር ሃይሉን ለማንሰራራት እገዛ ታድርግ እንጂ፣ በረጅም ግዜ እቅዷ የጦር መርከቦቹን የመምረጥ፣ መሳርያ ተከላ፣ ተያያዥ ድጋፍና ስልጠና ወዘተ በረጅም ጊዜ ተጠቃሚ እንደሚያረጋት በማሰብ ነው።

የባህር ሃይልና አብረውት የሚገዙት የጦር መርከቦች ብዙ ወጭ የሚጠይቁ ናቸው። በአለም ላይ ካሉ የጦር መርከቦች በመነሳት አንድ መርከብ ከ 50 ሚሊዮን ዶላር እስከ ትልልቆቹ 1 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃሉ። ይህም የመግዣውን ወጭ እንጂ በአገልግሎት ላይ እያሉ የሚያስፈልጋቸውን ጥገና ወጭ (maintenance cost) አይጨምርም። ጠ/ሚ አብይ የባህር ሃይሉን በጀልባ ለማቋቋም ካላሰቡ በስተቀር (በጀልባ ደግሞ የትም ርቀው መሄድ አይችሉም)፣ በምን ያህል ቢሊዮን ዶላር ለጨዋታ እያዘጋጅዋት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። ገንዘቡ በብድር ይምጣ በእገዛ፣ በኔ ምልከታ ይህ ገንዘብ ለሌላ ነገር ቢውል የሃገሪቷን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ይቀርፋል።

እውን የባህር ሃይል ያስፈልጋል?

ባህር ሃይሉን እንደገና ለማንሰራራት ያስፈለገበት ምክንያት ተብሎ በመንግስት በኩል ሲገለጽ የምንሰማቸው ምክንያቶች፣ ኢትዮጵያ ባህር ላይ ያላትን ጥቅም ለማስከበር፣ አስራ አንድ የሚሆኑ የንግድ መርከቦቻችንን ለመጠበቅ፣ ከውጭ ሃይል ሃገሪቷን ለመጠበቅ፣ አንኳር ተብለው የሚነሱ ምክንያቶች ናቸው። አንድ ባንድ እንያቸው።

የባህር ላይ ጥቅም ማስከበር በተመለከተ ኢትዮጵያ በአሁን ሰአት ወደብ አልባ ሃገር ከመሆኗ ጋር በተያያዘ የስጋት ምንጭ የሚሆን የውሃ ድንበር (coast line) የላትም። ስለዚህም ከባህር ጋር በተያያዘ የምታገኘው ጥቅም የለም ማለት ያስደፍራል። አለም አቀፍ የውሃ አካላትን (international waters or high seas) እንኳን ለመድረስ የሌሎችን ሃገራት ውሃ አካል ማቋረጥ አለባት። አገር ውስጥ ብዙ ያልተነኩ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሃገር አለም አቀፍ የውሃ አካላትን ጥቅም አስከብራለሁ ብላ የባሀር ሃይል ስታቋቁም ከመሳለቂያ ያለፈ ለድሃው ህዝብ የሚጠቅም ነገር አናተርፍም።

የንግድ መርከቦቻችንን ለመጠበቅ የሚለው ምክንያት ከሁሉም የወረድ ተራ ምክንያት ነው። አስራ አንዱ መርከቦች የሃገሪቷን 10% ጭነት እንኳን አያመላልሱም። ምናልባትም አስራ አንዱን መርከብ መሸጥ ይቀለል እነሱን ለመጠበቅ የባህር ሃይል ከማሰማራት። እስከ አሁንም እንዚሁ መርከቦቹ ያን ያህል ጠባቂ ቢያስፈልጋቸው ኖር እስከ አሁን ስራ አቁመው ነበር። ነገር ግን በደህንነት ስጋት ከስራ የተስተጓጎሉበት ግዜ የለም። በተጨማሪም ከ ዋጋ አንጻር ስናይ፣ አስራ አንዱ መርከቦች አሁን ባላቸው ዋጋ (current market value) ሁሉም ተሽጠው አንድ ደህና የጦር መርከብ መግዛት አይችሉም። በሌላ አባባል በቢሊዮን ዶላሮች የሚቋቋም የባህር ሃይል በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ የንግድ መርከቦችን ሊጠብቅ ነው ማለት ነው። ቀልድ ነው።

ከውጭ ሃይል ለመከላከል የሚለው ምክንያት ከሌሎቹ ውሃ የሚያነሳ ቢሆንም፣ አገሪቷን ከሚዘፍቃት እዳ ዳር ሲወዳደር ወቅታዊ ምክንያት ነው ለማለት አያስደፍርም። ብግልጽ አንናገርው እንጅ አንደኛ ስጋታችን ከግብጽ እንደሆነ መገመት ከባድ አደለም። ሆነም በአሁን ሰአት ከግብጽም ሆነ ከሌላ ወገን የሚታይ ስጋት (threat) የለም። ስጋቱ ቢኖር እንኳን የባህር ሃይል አቋቁሞ ወደ ሙሉ ዝግጁነት ለማድረስ አመታት በሚፈጅብት ሁኔታ፣ የባህር ላይ ስጋት ተወገደ ማለት አይደለም። የስነልቦና ጦርነትም (psychological warfare) ከሆነ፣ ግብጽም ሆነች ሌላ ሃገር በኢትዮጵያ ባህር ሃይል መቋቋም የሚመጣባቸው የስነልቦና ተጽእኖ የሚኖር አይምስለኝም። ምናልባትም በስነልቦና የተጀመረው ጦርነት ወደ እውነተኛ ጦርነት ሊጋጋል ይችላል። በጦር መፈርጠምን የሚመርጥ መንግስት ለሌላ የሰላማዊ አማራጭ መንገዶች የተጋረደ ነው የሚሆነው።

የውክላና ጦርነት

እውነተኛው ነገርግን ከብዙሃኑ የተደበቀው ምክንያት ሃገሪቷን ለውክልና ጦርነት ለማዘጋጀት ነው። ኢትዮጵያ እስከ አሁን የማትነሳበት አንድ ነገር ቢኖር የውክልና ጦርነት (proxy war) ነው። የጠ/ሚ አብይ የባህር ሃይልን ለማንሰራራት የሚደረግ ሩጫ በሌሎች ሃገራት የምንፈራውን የውክልና ጦርነት ቤት ድረስ መጋበዝ ነው። በሌሎች ሃገራት የምናየውን የውክልና ጦርነት፣ በሶርያ እና የመን የሚታየውን አይነት፣ የሌሎች ሃያላን ሃገራት ጦርነት አስፈጻሚ ለመሆን የሚደረግ እሽቅድድም ነው።

ፈረንሳይ ለረጅም አመታት በጅቡቲ ላይ የጦር ሰፈር መስርታ መቆየቷ ይታወቃል። አሁን ግን እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራትን በእርዳታ ስም በማማለል፣ የውክልና ጦርነት ፍላጎታቸውን በሌላ ሃገር ማስፈጸም ይፈልጋሉ። እንደ ራሽያ፣ፈረንሳይና ኖርዌይ ለባህር ሃይሉ መቋቋም አሻራቸውን ያሳረፉ ሃገራት ነገ በፈለጉት መንገድ የባህር ሃይሉን በሪሞት ከማዘዝና ወደ ፈለጉት የጦርነት አውድማ ከመጎተት የሚመልሳቸው ነገር የለም።

በሰላም ስም የኖቤል ሽልማት የተሸለሙት መሪያችን፣ ሰላም በሚሰብከው አፋቸው ለምን የጦር ጉልበት ማፈርጠም እንደፈለጉ ከሳቸው ውጭ ለማንም ግልጥ አይደለም። በአንድ ወገን ባህር ሃይሉ ራሽያ እየሰለጠነ፣ በሌላ ጎራ ደግሞ ከምእራባውያን በሚደረግ መጽዋእት የሚቋቋመው የባህር ሃይል ለሃገሪቷ የከፋ ቀውስ እንደሚያመጣ ለማየት ይሳናቸውል ብዬ ባላሰብም ባልጠበቅነው መንገድ ግን ሃገሪቷን የማያገባት የጦር አውድማ ላይ ጎትቶ እንደሚያስገባት እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።

በብልጽግና ከፍታ ስም

በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ አሁን ያልታየ በብልጽግና ከፍታ ስም ያልተዘረፈ የሃገር ሃብት የለም። በተለያዩ ግዜ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸው ወደ ስራ የተገቡ ነገር ግን ድሃውን ህዝብ ለእዳ የዳረጉ ፕሮጀክቶች አይተናል። ለምሳሌነት፣ የስኳር ፕሮጀክት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት፣ የባቡር ፕሮጀክት (የቀላሉም የከባዱም)፣ የሜቴክ ለቁጥር የሚታክቱ ፕሮጀክቶች፣ ሌላም ሌላም። እነዚህ ሁሉ ፕሮጀክቶች የሚያመሰስላቸው አንድ ነገር አለ፣ ብዙ ተስፋ ሰንቀው የመጡ ነገር ግን ለከፍተኛ ሙስናና ኪሳራ የዳረጉ ፕሮጀክቶች ናቸው። የባህር ሃይሉም ከዚህ የተለየ አይሆንም። በከፍተኛ ድግስና ሽርጉድ ወደ ስራ የተገባባቸው ሁሉም ፕሮጀክቶች አገሪቷን ወደ ከፍታ ሳይሆን ወደ አዘቅት ነው የከተቷት። ፕሮጀክቶቹ ጥቂት ሰዎችን ከማበልጸግ ውጭ ለድሃው ህዝብ ያመጡት ጥቅም ምንም የለም።

መግቢያ ላይ እንደመንደርደሪያ ያቀረብኩት የቀድሞው የባህር ሃይላችን የመጨረሻ ጊዜያት የሚያስተምሩን ብዙ ቁም ነገሮች አሉ። ባንድ በኩል የራሷ መተንፈሻ በር የሌላት ሃገር፣ የባህር ሃይሏን በየቦታው ስትጎትት መጨርሻ ላይ ለስም የማይመች ውድቀት መጋበዝ ነው። ሁለተኛ ጅቡቲ እንደከዚህ በፊቱ ጥቅሟን ካጣች የኛን የባህር ሃይል ከመበተን ወደ ኋላ አትልም። በአሁን ሰአት ጅቡቲ የኢትዮጵያ ማንቁርት (chocking point) መሆንዋን፣ የባህር ሃይሉን ስንጨምርላት የመደራደሪያ ጉልበት (bargaining power) እንደሚሆናትና የፈለገችውን ከመጠየቅ እንደማትመለስ ነው። ልንመካበት የፈለግነው የባህር ሃይል በማንም ሃገር ላይ በትነነው ነገ የጥንካሬያችን ሳይሆን የድክመታችን ምንጭ ነው የሚሆነው።

ወደ ሃገር ውስጥ ስንመለስ፣ በአሁን ሰአት ሃገሪቷ እንደ ሃገር መቀጠል በሚያሰጋት ሰአት፣ የውስጥ ችግሯ አፍጦ ሰው ከቤቱ ውጭ ምንም ደህንነት በማይሰማው ሰአት፣ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል መዘዋወር ልክ በመኖር እና ያለመኖር መካከል መምርጥ እስከሚምስል ድረስ፣ ጠፈር ላይ የላክናት ትንሽ ሳተላይት ምህዋሯ ላይ ሳትደርስ ከመሬት ስር ወገን በወገኑ ላይ አሳፋሪ ነገር ሲፈጽም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወይ ተፈናቅለው ወይ የእለት ምግባቸውን አጥተው የሞት ቀን ሲቆጥሩ፣ መንግስት (በፍትሃዊ መንገድ ያልተመረጠ መንግስት) ግን ባህር ሃይል ምልሶ ማቋቋም በሚል ከንቱ ቅዠት ሃገሪቷን ወደ አላስፈላጊ እዳ፣ ብሎም የውክልና ጦርነት እያዘጋጃት ነው።

እዚህ እይታ ላይ የቀረበው ሃሳብ እንደ ተራ ዜጋ ነገሮችን በማመዛዘን ብቻ ነው። በሌላ ብሎግ (http://ethiopiamaritimelogistics.com/2018/12/01/rebirth-of-ethiopian-navy-emotions-vs-rational-thinking/) የዛሬ አመት አካባቢ ሃሳቤን አጋርቼ ነበር። ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ላመዳበር ይረዳ ዘንድ ሊንኩን እዚህ ላይ አስፍሬዋለሁ።

5 Comments

 1. In short the same argument would have applied to HIM’s government on the very first inception of the Imperial Navy be ause of the national, economic and military capacities of Ethiopia then. Reality took hold only due to support garantees from super powers. Ethiopia was also a landlocked country then. The one valid factor that stands today as well is the Sea outlets. För the purpose of this discussion we all are in the dark about the unfolding revelations of Eritrean and Ethiopian relations looking forward. Ethiopia’s PM is far too intelligent to committ on a “fancy” dream project of this scale unless he has his reasons to leave out information that makes sense. In conclusion every project is risky, costly and unprofitable up to a stage where it takes off – the successes of nation building attests to the facts.

  Like

  1. Hi Mathew, thank you for your comment. I think comparing HIM time with the current situation is unfair. First, In HIM time, Ethiopia was having coastal area and sea ports (though annexation of Eritrea was legal or not- that is another debate). Hence the Imperial navy, and the Derg Navy later, were enjoying the full benefit of home-ports like Massawa and Assab. But current situation is different: there is no sea port that the country owns. It is in short near to impossible to set up navy force in another country where we do not have control. Besides being a logistical nightmare, It is going to cost billions of dollars. Second, the country is witnessing unseen political tension within the country. Our enemy is inside the country. Instead of focusing in stabilising the country, bringing coexistence, order and peace, the government attention is diverted unnecessarily to resurrecting the navy. The same money would have been used to stimulate our economy, create jobs and save the country from political chaos. Third, I respect your faith in PM Abiy, yet I have started questioning his ability to identify key priorities. He is incapable of enforcing rule of law within the country, yet he is busy setting up navy force in international waters. He keeps shuffling hundreds of ideas at a time but the country is failing miserably as a nation. In short, my point here is to show that resurrecting the navy is going the country a lot and that too at the wrong time. Lets concentrate in stabilising the country. That is what’s needed for millions of people caught in the cross fire of ethnic division.

   Like

 2. Selam Yigazu . Again, the question of Eritrea rejoining Ethiopia under federation driven by UN auspicious was not even in the cards when Admiral Iskinder Desta attended Dartmouth Academy. As for your negative confidence in Abiy’s suitability or ability, IT HAS NO PLACE IN YOUR ANALYSIS as this is a separate title and your judgement, unduly clouded by motives uncharacteristic of an analyst, leaves much to be desired, AS THE SITUATION DESCRIBED, THOUGH VALID, IS A PHENOMENA 30 YEARS IN THE BAKING. Like many “know it all” self styled critiques, you instead chose to hold him unfit for the mess he inherited – when understanding and support could play a positive role in strengthening cohesion and sustaining hope, disunity, disparity , denunciation to re-enforce failed state is what you are offering. I only mentioned new realities offered by new peace deals with Eritrea – unknown at our level – and yet you open up a can of “annexation” worms, uncalled for under the discussion. Ethnic divisiveness is here to stay as Ethiopia, Djibouti and Eritrea are all concoctions of diversities, and, possibilities for a lasting deal is as real as total disintegration in the extreme spectrum. Now that we are all threatened with climate changes putting economic development and existential survival to the harshest test, it is not far fetched to hope for solutions based on cooperation instead of ethnicity values. Finally and most importantly one might also add that the concept of “logistics and Maritime ” with a few cargo ships delivering 18% of the country’s import needs is more an economic drag festered on the weak national economy, considering the new lucrative and profitable options of integrating with the One Belt Road while augmenting maritime securities and protections instead, in a cooperative effort to enhance free flow of goods….from east to west of Africa’s belt and back… .

  Like

  1. I think you have problem organizing your thoughts. You are mixing things. First… it is up to you to blindly follow or worship the PM. I have no problem with that. My problem stems from the fact that the PM and his puppets are ignoring whats cooking within the country and yet the waste of money and energy that go into resurrecting the navy is devastating. At least this is not the right time. Second… I mentioned Eritrea annexation to support the reasoning that… unlike the current scenario, HIM imperial navy was having home ports (Assab and Massawa)… though annexation of Eritrea by itself is whole new topic. Third.. I am not sure why you brought climate change issue here? Fourth… 18% from where you got this figure? I only mentioned the fact that our 11 ships transport only 10% total cargo destined to Ethiopia. The remaining 90% of Ethiopian cargo is transported by foreign chartered ships. The country can manage better without the 11 oddly designed ships. Yet Abiy’s billion dollars navy is going to give protection to our million dollars ships. That is a joke. Last but not least… you brought the One Belt Road initiative topic here. I suggest you read further on OBR. Obviously you have no idea what is happening here.

   Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s